Skip to main content

ግላዊነት በ Microsoft

የእርስዎ ውሂብ፣ የእርስዎን ተሞክሮዎች ማጎልበት፣ በእርስዎ ቁጥጥር የሚደረግባቸው።

በMicrosoft ላይ፣ የእኛ ተልዕኮ በፕላኔቷ ላይ ያለን እያንዳንዱን ግለሰብ እና እያንዳንዱን ድርጅት ይበልጥ ስኬታማ እንዲሆን ማድረግ ነው። እኛ ይህንን ብልሃት የተሞላ ክላውድ በመገንባት፣ ምርታማነትን እና የንግድ ስራ ሂደትን ዳግም በመፍጠር እና በኮምፒዩተር መስራትን ይበልጥ ግላዊ በማድረግ በማከናወን ላይ እንገኛለን። በዚህ ሁሉ የግላዊነትን ጊዜ የማይሽረው እሴትን እንደነበረ እናቆያለን እንዲሁም የእርስዎን ውሂብ ለመቆጣጠር ያልዎትን ችሎታ በመጠበቅ ላይ እንሰራለን።

ይህም ውሂብ እንዴት እና ለምን እንደሚሰበሰብ እና ጥቅም ላይ እንደሚውል ትርጉም ያላቸው ምርጫዎችን እንዲያደርጉ እርስዎ መቻልዎን በማረጋገጥ ላይ እና በእኛ ምርቶች እና አገልግሎቶች ላይ በሙሉ ለእርስዎ ትክክለኛ የሆኑትን ምርጫዎች እንዲያደርጉ የሚያስፈልግዎትን መረጃ ማግኘትዎን በማረጋገጥ ስራ ይጀምራል።

በስድስት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቁልፍ የግላዊነት መርሆዎች ላይ በመመርኮዝ የእርስዎን አመኔታ ለማግኘት በየቀኑ በመስራት ላይ ነን፦

  • ቁጥጥር፦ ለመጠቀም ቀላል ከሆኑ መሳሪያዎች እና ግልጽ ምርጫዎች ጋር የእርስዎን ግላዊነት በእርስዎ ቁጥጥር ስር እንዲሆን እናደርጋለን።
  • ግልጽነት፦ ስለ ውሂብ አሰባሰብ እና አጠቃቀም በተመለከተ በመረጃ ላይ ተመርኩዘው ከውሳኔ ላይ መድረስ እንዲችሉ ግልጽ እንሆናለን።
  • ደኅንነት በጠንካራ መድን እና ምስጠራ በኩል እርስዎ ለእኛ በአደራ የሰጡንን ውሂብ ጥበቃ እናደርግለታለን።
  • ጠንካራ ሕጋዊ ጥበቃዎች፦ የእርስዎን ከባቢያዊ የግላዊነት ሕጎች እናከብራለን እንዲሁም እንደ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብት ለእርስዎ ግላዊነት ሕጋዊ ጥበቃ እንዲደረግ እንታገላለን።
  • ምንም ይዘትን የተመረኮዘ ዒላማ አደራረግ አይኖርም፦ የእርስዎን ኢሜይል፣ ውይይት፣ ፋይሎች ወይም ሌላ የግል ይዘት ወደ እርስዎ ማስታወቂያዎችን ዒላማ ለማድረግ አንጠቀምም።
  • ጥቅሞች ለእርስዎ፦ ውሂብን በምንሰበስብ ጊዜ እርስዎን ለመጠቀም እና የእርስዎን ተሞክሮ የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ እንጠቀምበታለን።

እነዚህ መርሆዎች የ Microsoft ን የግላዊነት አያያዝ መሰረታዊ መርሆዎችን ይመሰርታሉ እና የእኛን ምርቶች እና አገልግሎቶች የምንገነባበትን መንገድ መቅረጻቸውን ይቀጥላሉ። ለኢንተርፕራይዝ እና ቢዝነስ ደንበኞች፣ የእርስዎን ውሂብ እንዴት ጥበቃ እንደምናደርግለት ለማየት የ Microsoft የታመኑ ማዕከልMicrosoft Cloud ውስጥ ይፈትሹ።

በዚህ የድር ጣቢያ የተቀረው ክፍል ላይ ለእርስዎ ትክክለኛዎቹን ውሳኔዎች መወሰን እንዲችሉ ተጨማሪ መረጃ እና መቆጣጠሪያዎችን የሚሰጡ አገናኞችን ያገኛሉ። እንዲሁም በቀጣይነት ለመሻሻል በመስራት ላይ ነን፤ ስለዚህ በእኛ ምርቶች እና አገልግሎቶች ላይ ግላዊነትን በተመለከተ እርስዎ እንደሚጠብቁት የማይሰራ ነገር ሲያገኙ እባክዎ እኛ እንድናውቀው ያድርጉን


Microsoft ምን ዓይነት ውሂብ ይሰበስባል?

Microsoft እርስዎ ተጨማሪ ነገሮችን ማድረግ እንዲችሉ ለማገዝ ውሂብ ይሰበስባል። ይህን ለማድረግ፣ የእኛን ምርቶች፣ አገልግሎቶች፣ እና መሳሪያዎች ለማቅረብ እና ለማሻሻል፣ ግላዊነት የተላበሱ ተሞክሮዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ እንዲሁም እርስዎ ደህንነትዎ እንደተጠበቀ እንዲቆዩ ለማገዝ የምንሰበስበውን ውሂብ እንጠቀምበታለን። እኛ የምንሰበስበው ውሂብ በብዛት የተለመዱ ምድቦች መካከል የተወሰኑት እነዚህ ናቸው።

የድር አሰሳ አደራረግ እና የመስመር ላይ ፍለጋዎች

ድር ላይ እያሰሰች እና ፍለጋ እያደረገች ያለች ሴት

ለእርስዎ የተሻሉ የፍለጋ ውጤቶችን ለመስጠት እንደ አብዛኛዎቹ የፍለጋ ፕሮግራሞች ሁሉ፣ የእርስዎን የፍለጋ ታሪክ፣ እና ከሌሎች ሰዎች የተውጣጣውን ታሪክ እንጠቀማለን። የድር አሰሳ አደራረግን ለማፍጠን፣ እርስዎ መሄድ የሚፈልጉበትን አስቀድሞ ለመገመት እንዲቻል የ Microsoft ድር አሳሾች የአሰሳ አደራረግ ታሪክን ሊሰበስቡ እና ሊጠቀሙ ይችላሉ። Cortana በእርስዎ የአሰሳ አደራረግ እና የፍለጋ ታሪክ ላይ በመመርኮዝ ግላዊነት የተላበሱ ምክሮችን ልትሰጥ ትችላለች።

የአሰሳ ታሪክዎ በዳያግኖስቲክዎች እና የግብረመልስ ቅንብር በኩል እንዲሰበሰብ ወይም እንዳይሰበሰብ በWindows ግላዊነት የክንውን አውዶችዎ ውስጥ መምረጥ ይችላሉ። በተጨማሪ Cortana ወደ ለፍለጋዎ እና የአሰሳ ታሪክዎ መዳረሻ ይኑራት አይኑራት በCortana እና Microsoft Edge የክንውን አውዶች ውስጥ ማስተዳደር ይችላሉ።

እርስዎ የሚሄዱባቸው ቦታዎች

በአይስክሬም መሸጫ መደብር አጠገብ መኪና መንዳት

የመገኛ አካባቢ መረጃ እርስዎ ሊሄዱ ስለሚፈልጉባቸው ቦታዎች አቅጣጫዎችን ለእርስዎ ለመስጠት እና አሁን ስላሉበት ቦታ ተዛማጅነት ያለውን መረጃ ለእርስዎ ለማሳየት እንድንችል ያግዘናል። ለዚህ ሲባል፣ እርስዎ የሚሰጡዋቸውን መገኛ አካባቢዎች ወይም እንደ GPS ወይም IP አድራሻዎች የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ፈልገን ያገኘናቸውን መገኛ አካባቢዎች እንጠቀማለን።

መገኛ አካባቢን ፈልጎ ማግኘት በተጨማሪ ለእርስዎ ጥበቃ እንድናደርግ ያግዘናል። ለምሳሌ፦ ከቶኪዮ ሁልጊዜ በሚቻል መልኩ በመለያ የሚገቡ ከሆነ እና ድንገት ከለንደን በመለያ ቢገቡ በእርግጠኝነት እርስዎ ራስዎ መሆንዎን ለማረጋገጥ እንችላለን።

በየክንውን አውዶች > ግላዊነት > አካባቢ ውስጥ ለመሳሪያዎ የአካባቢ አገልግሎቶችን ማብራት ወይም ማጥፋት ይችላሉ። ከዚህ ላይ ሆነው፣ በተጨማሪ የትኛዎቹ የመተግበሪያዎች ወደ የአካባቢዎ መዳረሻ እንደሚኖራቸው እና በመሳሪያዎ ላይ የተከማቸውን የአካባቢ ታሪክ ማስተዳደር እንደሚችሉ መምረጥ ይችላሉ።

በግል፣ እርስዎን ለመርዳት የሚያግዘን ውሂብ

በእግረኛ መንገድ ላይ ስልኩን የሚያይ ሰው

ትራፊክን ማስወገድ እንዲችሉ፣ የልደት ቀኖችን እንዲያስታውሱ፣ በእርስዎ እውቂያ ዝርዝር ውስጥ ትክክለኛውን “ሰላማዊት” የሚል ስም መጻፍ እንዲችሉ እና በአጠቃላይ ተጨማሪ ነገሮችን እርስዎ ማድረግ እንዲችሉ ለማገዝ፣ Cortana የእርስዎ ዝንባሌ ምን እንደሆነ፣ በእርስዎ የቀን መቁጠሪያ ውስጥ ምን እንዳለ፣ እና ከማን ጋር ነገሮችን ማድረግ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ትፈልጋለች። ወደ የእርስዎ የቁልፍ ሰሌዳ መድረስ በማይፈልጉበት ጊዜ፣ እርስዎ የሚናገሩትን ለመተርጎም ወይም በሰነዶች እና በጽሑፍ መልዕክቶች ላይ ለመጻፍ እርስዎን ለማገዝ የእርስዎን ንግግር እና የእጅ ጽሑፍ አጣጣሎችን መጠቀም እንችላለን።

በግላዊነት ዳሽቦርድዎ ላይ የእርስዎን የCortana ፍላጎቶች እና ሌላ ውሂብን ያስተዳድሩ

ይበልጥ አስደሳች የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት የምንጠቀምበት ውሂብ

በመንገድ ላይ የምትሄድ ሴት

አንዳንድ የMicrosoft አገልግሎቶች በማስታወቂያ የሚደገፉ ናቸው። እርስዎ ፍላጎቱ ሊኖርዎት የሚችልባቸውን ማስታወቂያዎች ለማሳየት እንደ የእርስዎ መገኛ አካባቢ፣ የ Bing ድር ፍለጋዎች፣ እርስዎ የተመለከቱዋቸው የ Microsoft ወይም የማስታወቂያ አስነጋሪ የድር ገጾች፣ ስነ ሕዝብ መረጃዎች እና እርስዎ ተወዳጅ ያደረጉዋቸው ነገሮችን የመሳሰለ ውሂብን እንጠቀማለን። ማስታወቂያዎችን ወደ እርስዎ ዒላማ አድርጎ ለመላክ በኢሜይል፣ በውይይት፣ በቪዲዮ ጥሪዎች ወይም የድምጽ ኢሜይል ወይም በእርስዎ ሰነዶች፣ ፎቶዎች ወይም ሌላ የግል ፋይሎች ውስጥ እርስዎ የሚሉትን ነገር አንጠቀምም።

በእርስዎ ዝንባሌ ላይ በመመርኮዝ Microsoft ለእርስዎ ማስታወቂያዎችን ማሳየቱን ለማስቆም የእኛን የማስታወቂያ ማስነገር ስራ መቆጣጠሪያዎች መስመር ላይ ይጠቀሙ። እንዲህም ሆኖ ማስታወቂያዎችን ማየትዎን ሊቀጥሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን እርስዎ እንደሚፈልጉዋቸው ዓይነቶች አይሆኑም።

በመለያ መግባት እና የክፍያ ውሂብ

ለጠጣው ቡና እየከፈለ ያለ ሰው

ለራስዎ የ Microsoft መለያ መመዝገብ እንደ ማከማቻ እና የቤተሰብ የክንውን አውዶች የመሳሰሉ የመስመር ላይ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ያስችልዎታል፣ እንዲሁም በመሳሪያዎች ላይ በሙሉ የእርስዎን የክንውን አውዶች በማመሳሰል ውስጥ እንዲያቆዩ ያግዝዎታል። ወደ የእርስዎ መለያ የመክፈያ ውሂብ በሚያክሉበት ጊዜ፣ በእርስዎ የ Windows 10 መሳሪያዎች ላይ መተግበሪዎችን፣ የደንበኝነት ምዝገባዎችን፣ ፊልሞችን፣ ቲቪ እና ጨዋታዎችን ማግኘት ቀላል ነው።

የእርስዎን የይለፍ ቃል ምስጢራዊ አድርጎ በማቆየት እና እንደ የእርስዎ ስልክ ቁጥር ወይም የኢሜይል አድራሻ የመሳሰሉ ተጨማሪ ትርፍ የደህንነት መረጃ በማከል የእርስዎን ፋይሎችን፣ ክሬዲት ካርዶች፣ የአሰሳ አደራረግ ታሪክ፣ እና የግአኛ አካባቢ መረጃን ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተቀባይነት ያለው ማድረግ ይችላሉ።

የይለፍ ቃሎችን፣ የደህንነት መረጃን፣ እና የክፍያ አማራጮችን ለማዘመን፣ Microsoft መለያ የድር ጣቢያ የሚለውን ይጎብኙ።


Windows 10 እና የመስመር ላይ አገልግሎቶችዎ

Windows 10 ዓርማ
ላፕቶፕ የምትጥቀም ዴስክ ላይ ቁጭ ያለች ሴት

በWindows 10 በክላውድ የጎለበት አገልግሎት በመጠቀም፣ ውሂብ የእርስዎን ተሞክሮ በቀጣይነት እንድንጠብቅ እና እንድናሻሽል ያግዘናል። ለምሳሌ፦ መስመር ላይ ደህንነትዎ እንደተጠበቀ እንዲቆዩ ለማገዝ፣ ለሚታወቅ ማልዌር በራስሰር የWindows 10 መሳሪያዎችን እንቃኛለን። መሳሪያዎ በጥሩ ሁኔታ መስራቱን እንዲቀጥል፣ የWindows 10 ስርዓትዎ በምን መልኩ ስራውን እያከናወነ እንዳለ ለማወቅ በቀጣይነት መረጃን ለመቀበል፣ በተጨማሪነት የዳያግኖስቲክ ውሂብ እንሰበስባለን። ስለዚህ ከአንድ የተወሰነ የአታሚ አንጻፊ ጋር የሆነ ችግር እንዳለ ካወቅን፣ ያንን የመሰለ አታሚ ለሚጠቀሙ ሰዎች ብቻ ትክክለኛዎቹን አንጻፊዎች እንልክላቸዋለን።

ግላዊነት የተላበሱ አገልግሎቶችን እና ተሞክሮዎችን በ Windows 10 ውስጥ ለማቅረብ መረጃ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ለመቆጣጠር የሚያስችሉ በርካታ መቆጣጠሪያዎችን በተጨማሪ እንሰጥዎታለን። የWindows 10 የግላዊነት የክንውን አውዶችዎን ከመሰረታዊ ዳያግኖስቲክ ውሂብ እስከ ግላዊነት የተላበሱ አገልግሎቶች ድረስ በማንኛውም ጊዜ ወደ የክንውን አውዶች > ግላዊነት > ዳያግኖስቲክዎች እና ግብረመልስ በመሄድ ለሁሉም ነገር ማስተካከል ይችላሉ።

ተሞክሮዎን ግላዊነት ለማላበስ እያንዳንዱን ምርቶቻችንን እንዴት ውሂብ እንደሚጠቀሙ ይወቁ።

Office Office logo

በማንኛውም የOffice መተግበሪያ ውስጥ ወደ ፋይል > መለያ > የግላዊነት መለያ በመሄድ የግላዊነት የክንውን አውዶችን ይመልከቱ።

የመለያ የግላዊነት የክንውን አውዶች

Skype Skype አርማ

የእርስዎን መገለጫ Skype ውስጥ እና Skype.com ላይ ባሉ ሌሎች የግላዊነት የክንውን አውዶች አማካኝነት ማን ማየት እንደሚችል አርትዕ ያድርጉ።

Skype የክንውን አውዶች

OneDrive OneDrive logo

የእርስዎን ፋይሎች በ OneDrive ላይ ማን ማየት እንደሚችል መቆጣጠር ይችላሉ።

የእርስዎን ፋይሎች ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ለማቆየት የተሻሉ አሰራሮች

Xbox Xbox አርማ

የእርስዎን የXbox የግላዊነት የክንውን አውዶች በእርስዎ ኮንሶል ወይም Xbox.com ላይ ያስተካክሉ።

Xbox የግላዊነት የክንውን አውዶች

Bing Bing አርማ

ወደ Bing.com በመለያ በመግባት የፍለጋ ጥቆማዎችን ያጥፉ እንዲሁም ሌሎች የክንውን አውዶችን ያስተካክሉ።

Bing የግላዊነት የክንውን አውዶች

Cortana Cortana አርማ

Cortana ከመሳሪያዎ እና ከሌሎች የMicrosoft አገልግሎቶች ላይ በመለያ መግባትን እና ውሂብ መጠቀምን በሚፈቅዱ ጊዜ የተሻለ ትሰራለች።

የCortana የክንውን አውዶች

በምርቶቻችን ውስጥ ስለ ግላዊነት ተጨማሪ መረጃ፣ እባከዎ የ Microsoft የግላዊነት ማዕከል ይመልከቱ።